ስለማር አስገራሚ እውነታዎች

8 Mons Ago 571
ስለማር አስገራሚ እውነታዎች
  • በዓለም ላይ ከ300 በላይ የማር ዓይነቶች አሉ።
  • ማር በንጽህና ከተያዘ ሳይበላሽ ብዙ ጊዜ በመቆየት በዓለም ቀዳሚው ምግብ ነው።
  • ማር ለባክቴሪያዎች እና ለሌሎች በዓይን የማይታዩ ተህዋሲያን መኖሪያነት ተስማሚ አይደለም።
  • የፋኦ ሪፖርት እንደሚያመለክተው፥ ቻይና በዓለም ቀዳሚዋ ማር አምራች ሀገር ናት፤ ቱርክ እና ኢራን ደግሞ ይከተላሉ።
  • ከማር ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ በማግኘት ግን ኒውዝላንድ ቀዳሚ ናት።
  • የማር ጣዕም ንቦች በብዛት በሚቀስሙት የአበባ ዓይነት ይወሰናል።
  • ማር ከምግብነት ባለፈ ለብዙ በሽታዎች መድኃኒትም ነው።
  • ማር ቁስል ላይ ሲደረግ ኢንፌክሽንን ይከላከላል፤ የመዳን ሂደትንም ያፋጥናል።
  • ንቦች እድሜን እና ጾታን መሰረት ያደረገ የስራ ክፍፍል አላቸው። ከእነዚህም ውስጥ እጪዎችን የሚንከባከቡ፣ ቀፎውን ከጥቃት የሚጠብቁ እና ማር ለመስራት አበባ የሚቀስሙ ይገኙበታል።
  • የንግስት ንቦች አማካኝ ዕድሜ ከ1 እስከ 2 ዓመት ሲሆን፤ የሰራተኛ ንቦች ዕድሜ በክረምት ከ15 እስከ 38 ቀናት፣ በበጋ ደግሞ ከ150 እስከ 200 ቀናት ነው።
  • አንዲት ንብ በሕይወት ዘመኗ አንድ ማንኪያ መጠን ያለው ማር ትሰራለች።
  • ንግስት ንብ በሕይወት ዘመኗ ከ800 ሺህ በላይ እንቁላሎችን (እጪዎችን) ትጥላለች።
  • ንቦች በጣም ጠንቃቃ እና ንጽህና የሚወዱ ፍጥረታት ናቸው። ንቦች የራሳቸውንም የቀፎአቸውንም ንጽህና ይጠብቃሉ።
  • ንቦች የሚግባቡት ዳንስ በሚመስሉ ለየት ባሉ እንቅስቃሴዎች ነው።
  • ንብ 5 ዓይኖች፣ 4 ክንፎች እና 6 እግሮች አሏት።
  • ንቦች በቀን በአማካኝ ከ5 እስከ 8 ሰዓት ይተኛሉ። ንቦች በአብዛኛው የሚተኙት ሌሊት ነው።
  • ንቦች አበባ ለመቅሰም ከቀፎአቸው እስከ 8 ኪ.ሜ ርቀው ሊጓዙ ይችላሉ።

በኢዮብ መንግሥቱ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top