የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲፕሎማሲን በመጠቀም ኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበትን ዕድል ማመቻቸት እንዳለባቸው ተገለፀ

4 Mons Ago
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲፕሎማሲን በመጠቀም ኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበትን ዕድል ማመቻቸት እንዳለባቸው ተገለፀ

ይህ የተገለፀው ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ቀጣና ያላት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ላይ ያተኮረ በ5 ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እየተካሔደ ባለበት ወቅት ነው።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ፥ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ ዲፕሎማሲን በተከተለ መንገድ መልስ እንዲያገኝ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሊሰሩ ይገባቸዋል ብለዋል።

ተጠባባቂ ፕሬዚዳንቱ ኢትየጵያውያን በቅርብ ርቀት ከሚመለከቱት የባህር በር ፍትሐዊ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባቸው ጠቅሰው፤ የህዝብ ለህዝብ እና የባህል ዲፕሎማሲን ማሳደግ ከዩኒቨርሲቲዎች ይጠበቃል ብለዋል።

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሐመድ ኡስማን ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የባህር በር ለማግኘት ያላትን ትክክለኛ ፍላጎት በማሳወቅና ሌሎች አካላት የሚሰነዝሩትን ሀሰተኛ መረጃ በማክሸፍ በኩል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

በ5 ዩኒቨርሲቲዎች ትብብር በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ላይ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ቀጣና ያላት ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ላይ ያተኮሩ ጥናቶች እየቀረቡ ነው።

ኢትጵዮጵያ ወደብ አልባ በመሆኗ ሸቀጦችን ለማስገባትም ሆነ ምርቶችን ወደ ውጪ ለመላክ ያልዳበረ መሰረተ ልማት ባላቸው ጎረቤቶቿ ላይ ጥገኛ እንድትሆን ማድረጉም ተጠቅሷል።

የቀይ ባሀር ቀጣናን ከፉክክር ወደ ትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት እድሎችን በማሳደግ  የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማረጋገጥና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጠንካራ ስራ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ጥናታዊ መድረኩን ያዘጋጁት ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ፣ መቐለ፣ ድሬዳዋ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ነው።

በንብረቴ ተሆነ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top