ለብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

11 Mons Ago 171
ለብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ
ለብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተገነባው የመታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት መመረቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
 
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ፈር ቀዳጅ ከሆኑት መካከል አንዱ ሲሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆንም ሀገራቸውን አገልግለዋል።
 
በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት በተለያዩ የፖለቲካ ኃላፊነቶች በትጋት እና በቁርጠኝነት ያገለገሉት ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የልዩ ፍርድ ቤት ዳኛም ነበሩ።
 
ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በሊግ ኦፍ ኔሽን የኢትዮጵያ የመጀመሪያ ልዑክ አባልም እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
 
በዛሬው ዕለት በተካሄደው የመታሰቢያ ሐውልት ምረቃ መርሐ-ግብር ላይ የተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተወካዮች፣ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ተመራማሪዎች እና ደራሲያን፣ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ወዳጅ ዘመዶች እና ቤተሰቦች ተገኝተዋል። 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top