አትላንታ እና አዲስ አበባ ከተማዎች በኢንተርፕረነርሺፕ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ በባህል ለባህል ትሥሥር እንዲሁም በንግድ እና በቤት ግንባታ ላይ በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ደርሰዋል።
የአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲክሰን ከልዑክ ቡድናቸው ጋር በመሆን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ውጤታማ እንደነበር የገለጹት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ ግንኙነቱ ለኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በብዙ መልኩ ማስፋት የሚያስችል እንደሆነ ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ሰው ተኮር በማድረግ እና የፖለቲካ ሪፎርሙን በጠንካራ መሠረት ላይ በማኖር ኢትዮጵያን በቀጣይም የስህበት ማዕከል ለማድረግ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ብለዋል።
በኮሰን ብርሃኑ