የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የኢቢሲ ሰራተኞች ረቂቅ ደንብን ለዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መራ

1 Yr Ago
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የኢቢሲ ሰራተኞች ረቂቅ ደንብን ለዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መራ

የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ሰራተኞች ረቂቅ ደንብን ለዴሞክራሲያዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መራ።

ምክር ቤቱ በዛሬ መደበኛ ስብሰባው ሌሎች ሁለት ረቂቅ አዋጆችንም መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሰራተኞች ረቂቅ ደንብ ከስራው ባህሪ አንፃር በኮርፖሬሽኑና በሰራተኞች መካከል ያለውን የስራ ግንኙነት በግልፅና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲመራ ያለመ ስለመሆኑ ተነስቷል።

ሌላው ኮርፖሬሽኑ የጀመረው ሪፎርም እንዲሳካ የደንቡ መሻሻል በምክንያትነት ቀርቧል።

የምክርቤቱ አባላት የጋዜጠኞችን የስራ ደህንነት ማስከበርና የሙያ ነፃነት ላይ ደንቡ እንዲመለከተው አስተያየት ሰጥተዋል።

ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎ የማዕድን ሀብት ልማት ረቂቅ አዋጅንም መርምሮ ለኢንደስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ረቂቅ አዋጁ የማዕድን ልማት የአካባቢ ብክለት ፣ የማህበረሰብ ተጠቃሚነትና ተፅዕኖ ቁጥጥር ላይ ማየት እንደሚገባው በምክር ቤት አባላቱ አስተያየት ተሰጥቷል።

ሌላኛው ምክር ቤቱ የመንግስት ግዢና ንብረት ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለፕላን፣ ለበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ከሚቴ እንዲመለከተው መርቷል።

በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ አዋጁን ማሻሻል ያስፈለገበት ዘመናዊ የኤሌክትሮኒክ ግዢ ትግበራና ተጠያቂነትን ለማስፈን በማስፈለጉ ነው ብለዋል።

የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ግዢ ተቋማቱን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ለማካተት ስለመሆኑም አንስተዋል።

በሙሉ ግርማይ


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top