"የትግራይ ክልልን መልሶ ግንባታ ለማረጋገጥ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ ነው" - አቶ ጌታቸው ረዳ

1 Yr Ago
"የትግራይ ክልልን መልሶ ግንባታ ለማረጋገጥ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ ነው" - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ክልልን መልሶ ግንባታ ለማረጋገጥ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ያፀደቃቸው የክልሉ መልሶ ግንባታ እቅዶችንና አቅጣጫዎችን መሰረት በማድረግ ሲካሄድ የቆየው ክልላዊ መድረክ ተጠናቋል።

መድረኩ በትግራይ ክልል መልሶ ግንባታ ለማካሄድ ከክልል እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር የሚሰሩ እቅዶች ስትራቴጂዎችና አቅጣጫዎች ላይ የተሟላ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ታልሞ የተካሄደ ነው ተብሏል።

በመድረኩ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት፣ የወረዳና ከተሞች የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል።

በዚሁ ወቅት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የትግራይ ክልልን መልሶ ግንባታ ለማረጋገጥ ጊዜያዊ አስተዳደሩ እየሰራ ነው ብለዋል።

በዚህ መሰረት በክልሉ ከላይኛው እስከ ታችኛው የመንግስት መዋቅር ያለው አመራር በታያዙት ዕቅዶችና ስትራቴጂዎች ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ በቅንጅት መስራት ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

በተጨማሪም የትግራይ ክልልን ፖለቲካዊ ስነ ምህዳር የማስፋት ጉዳይ ለትግራይ ህዝብ የተሟላ ነጻነት ከማረጋገጥ ውጭ የሚያመጣው አሉታዊ ተጽእኖ እንደሌለም አብራርተዋል።

በዚህም በዴሞክራሲ ያሉትን ግድፈቶች ማሟላትና ማስፋት፣ ፍትሐዊ አስተዳደርን ማረጋገጥ ይገባልም ነው ያሉት።

ህዝብ የማይፈልገውን አመራር ልናስቀጥል አንችልም ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው፣ በአስተዳደር ያለ ችግር በአስተማማኝ ደረጃ እስከተፈታ ድረስ ሊንቀሳቀስ የሚችል አቅም እንዳለና የፋይናንስ ችግርንም ማቃለል እንደሚቻል መግለጻቸውን የክልሉ ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።"


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top