የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ

12 Mons Ago
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ኩባንያዎቹ በድምሩ 1.645 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንደሚያደርጉ ተገልጿል።
“ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” የኢንቨስትመንት ፎረም የማጠቃለያ መርሐ ግብር ተካሂዷል።
በሲሚንቶ ዘርፍ የተሰማራው የቻይናው ሲኖማ ኩንባያ በ500 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በሲሚንቶ ዘርፍ ላይ ለመሥራት ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ስምምነት መፈረሙ ተጠቅሷል።
ከሚሽኑ ሻን ከተሰኘው የቻይና ጣውላ እና የእንጨት ውጤቶች አምራች ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፤ በስምምነቱም ኩባንያው 1 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሚያወጡ 6 ዘርፎች ላይ ኢንቨስት እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በሌላ በኩል ከሚሽኑ ቼን ሺ ከተሰኘው የቻይና የቤት እና የቢሮ ዕቃዎች አምራች ኩባንያ ጋር ስምምነት የፈፀመ ሲሆን፣ በዚህም ኩባንያው በ8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የእንጨት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ እንደሚገነባ ተጠቅሷል።
ኮሚሽኑ ዩኒሊቨር እና አፍሪካ ኑትሪሽን ከሰተኘው ኩባንያ ጋር አዲስ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለማቋቋም የ45 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት መፈራረሙ ተጠቁሟል።
በተመሳሳይ ሁዋጂያን የተሰኘው የቻይና ኢንዱስትሪያል ፓርክ ፕሮጀክቶቻቸውን በፓርኩ ውስጥ መሠረት ለማድረግ ፍላጎት ካላቸው 21 የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
በፎረሙ ላይ “ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” ስኬታማ እንዲሆን ስፖንስር ላደረጉ ተቋማት ይፋዊ የእውቅና ሽልማት መሰጠቱንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top