በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ የተመራ የክልል ርዕሳነ መስተዳደር ልዑካን መቐለ ገብተዋል።
የሁሉም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮቹ እና የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የመቐለ ከተማ ነዎሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የርዕሳነ መስተዳደሮቹ የመቐለ ጉዞ ለትግራይ ክልል አጋርነታቸውን ለማሳየት እና በመልሶ ግንባታ ሂደት የድርሻውን ለማበርከት ዓላማ ያደረገ ነው።
የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮች፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባዎች ወደ መቐለ ሲያቀኑ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።