የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን ለኢትዮጵያ መንግሥት ምስጋና አቀረቡ

1 Yr Ago
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን ለኢትዮጵያ መንግሥት ምስጋና አቀረቡ
የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው የርዕደ-መሬት አደጋ ወቅት ላደረገው አፋጣኝ የነፍስ አድን ድጋፍ እና ትብብር ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
ፕሬዚዳንቱ በቱርክ ለኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ እና ለኢትዮጵያ የነፍስ አድን ቡድን መሪ ሌ/ጄኔራል ደስታ አቢቼ የሜዳሊያ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።
ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን በርዕደ-መሬት አደጋ ወቅት ድጋፍ ላደረጉ ሌሎች አገራትም የሜዳሊያ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ማበርከታቸውን በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top