አሜሪካ ዲፕሎማቶቿን ከሱዳን በማስወጣት ሒደት ኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ የሚመሰገን ነው፦ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

1 Yr Ago
አሜሪካ ዲፕሎማቶቿን ከሱዳን በማስወጣት ሒደት ኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ የሚመሰገን ነው፦ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ዲፕሎማቶቿን ከሱዳን በማስወጣት ሒደት ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ ምስጋና አቀረቡ።
በፕሬዚዳንቱ ትዕዛዝ መሠረት የአሜሪካ ሠራዊት አባላት የሀገሪቱን ዲፕሎማቶች በትላንትናው ዕለት ከካርቱም የማስወጣት ኦፕሬሽን አከናውነዋል።
በዚህ ሥራ የኢትዮጵያ መንግሥት እና የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ላደረጉት ድጋፍ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አመስግነዋል፤ ለአሜሪካ ድጋፍ ላደረጉ ጂቡቲ እና ሳዑዲ ዓረቢያም ምስጋና አቅርበዋል።
በሱዳን የተቀሰቀሰው አሳዛኝ ግጭት የበርካታ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፣ ይህ ተቀባይነት የሌለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።
በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ቲቦር ናዥ በበኩላቸው፣ "ኢትዮጵያ አሜሪካ ችግር ሲያጋጥማት በተደጋጋሚ ድጋፍ ያደረገች እውነተኛ ወዳጅ አገር ናት" ብለዋል።
አሁንም አሜሪካ ዲፕሎማቶቿን ከሱዳን በማስወጣት ሒደት ላደረገችው ድጋፍ አመስግነዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top