ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስሎቬንያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

1 Yr Ago
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስሎቬንያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስሎቬንያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታንጃ ፋጆን ጋር በዛሬው ዕለት ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ በኢትዮጵያ እና በስሎቬንያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ከሚኒስትሯ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
የስሎቬንያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታንጃ ፋጆን ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ኢትዮጵያ ይገኛሉ።
ሚኒስትሯ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸው ይታወሳል።

ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top