ለቦረና ድርቅ ተጎጂዎች እየተሰበሰበ ያለው ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ በተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ገቢ እንዲደረግ የኦሮሚያ ክልል ጥሪ አቀረበ። ክልሉ ይህን አስመልክቶ ያስተላለፈው ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል፥
በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በድርቅ ሳቢያ የደረሰውን ጉዳት ለመቀነስ የክልሉ መንግስት ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል፣ እየሰራም ይገኛል።
ይሁን እንጂ ለአምስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ ሳይዘንብ በመቆየቱ ለችግር የተጋለጡ እና እርዳታ የሚያፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ብቻ ችግሩን መፍታት አይቻልም፡፡
ይህንኑ ምክንያት በማድረግ በሀገር ውስጥ እና በውጪ ያሉ ግለሰቦች፣ አርቲስቶች፣ ታዋቂ ሰዎች እና ድርጅቶች ግለሰቦች በድርቅ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጠው የቦረና ህዝብ እርዳታ እያሰባሰቡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡
ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ እያደረጋችሁ ያላችሁት ጥረት የሚያስመሰግን ነው፤ በችግር ወቅት መረዳዳትና አብሮ መቆም ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጉዳይ ነው።
ይሁን እንጂ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ይህንን ጉዳይ ለማቀናጀት ከክልል እስከ ቀበሌ ድርስ ድጋፉን የሚያስተባብር መዋቅር የዘረጋ በመሆኑ፣ ለድጋፉ ገንዘብ የሚሰበሰብበት የሂሳብ ቁጥር የተከፈተ በመሆኑ እና እየተሰበሰበ ያለው ድጋፍ ተጠያቂነትና ኃላፊነት ባለው መልኩ እንዲሰበሰብ ብሎም ተጋላጩ ህዝብ ጋር እንዲደርስ በተለያየ አቅጣጫ ለተጎጂው ህዝብ እያሰባሰባችሁት ያለውን ገንዘብ ከዚህ በመቀጠል ባለው የባንክ የሂሳብ ቁጥር ታስገቡ ዘንድ እንጠይቃለን፡፡
የቡሳ ጎኖፋ የሂሳብ ቁጥር
ሲንቄ ባንክ፡ 1029565101201
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000007343756