የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ5 ፓርቲዎችን የማስጠንቀቂያ እግድ አነሳ

15 Days Ago 103
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ5 ፓርቲዎችን የማስጠንቀቂያ እግድ አነሳ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ (ዎ.ብ.ን)፣ አዲስ ትውልድ ፓርቲ (አ.ት.ፓ)፣ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋ.ህ.ዴ.ን)፣ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት (ኢ.ዴ.ህ) እና የአገው ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲን የማስጠንቀቂያ እግድ ማንሳቱን አስታውቋል።
 
ቦርዱ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠቅላላ ጉባዔ፣ ከኦዲትና በሴት አባላት ቁጥር አማካኝነት ከሚገኝ የገንዘብ ድጋፍ ጋር በተገናኘ 11 ፓርቲዎች ላይ የዕግድ ውሣኔ ማሳለፉ ይታወቃል።
 
ቦርዱ ከታገዱት ፓርቲዎች ውስጥ የይቅርታና የመከላከያ መልስ ያቀረቡትን የአምስቱን ፓርቲዎች ጉዳይ መመርመሩን አስታውቋል፡፡
 
በዚህም ፓርቲዎቹ ያለፈውን ስህተት እንደማይደግሙና በቀጣይም በሚያቀርቧቸው መረጃዎች ጥራት በመተማመን እንዲሁም የቦርዱን ሥራ ከሚያደናቅፍና ዕምነት ጥያቄ ውስጥ ከሚከቱ ተግባራት ተቆጥበው በሕግ አግባብ ብቻ እንደሚንቀሳቀሱ በማመን፤ በማስጠንቀቂያ ዕግዱን ያነሣ መሆኑን ነው ቦርዱ ባወጣው መረጃው ያስታወቀው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top