ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመረቀ

2 Mons Ago 522
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመረቀ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 2ሺህ 593 ተማሪዎች አስመርቋል።
ከተመራቂዎቹ መካከል 692 ሴቶች መሆናቸውን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ ገልጸዋል።
ተመራቂዎቹ በመደበኛው፣ በማታና በክረምት የስልጠና መርሐ-ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ከተመራቂዎቹ መካከል አንድ ሺህ 681 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ ቀሪዎቹ በሁለተኛና በሦስተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ እንደሆኑ አመልክተዋል።
በተጨማሪም በህክምናው ዘርፍ በ"ስፔሻሊቲና በሰብ ስፔሻሊቲ" ሰባት የጤና ባለሙያዎችም የምረቃው አካል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ዩኒቨርሲቲው የትምህርት እድል የሰጣቸው 68 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ተማሪዎች በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው ለምረቃ መብቃታቸውንም ፕሬዚዳንቱ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top