ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር በቻይና ተወያይተዋል።
ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ቻይና ሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል እና ላካሄዱት ጠቃሚ ውይይት ምስጋና አቅርበዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ የቻይናን ያልተቋረጠ ዘርፈብዙ ድጋፍ በእጅጉ ታደንቃለች ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል።
እንደ ሀገር የተለያዩ ተግዳሮቶችን ብናስተናግድም በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንደስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በቴሌኮሙኒኬሽን እና ሌሎች ዘርፎች ትርጉም ያላቸው የለውጥ ርምጃዎች ተራምደናል ብለዋል።
አያይዘውም በዚህ የእድገት ጎዳና የቻይና ኢንቨስትመንቶች ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ሲሉ ነው የገለጹት።
በቱሪዝም ብሎም በወረቀት እና እንደ ፐልፕ ያሉ ተያያዥ ግብዓቶች ኢንደስትሪንም ለማሳደግ እምቅ አቅም አለ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር በጽናት እንሰራለን ብለዋል።