ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሴሚናር በዘላቂ ልማት ግቦች ያላትን ተሞክሮ አካፈለች

4 Mons Ago 269
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ሴሚናር  በዘላቂ ልማት ግቦች ያላትን ተሞክሮ አካፈለች
ኢትዮጵያ በቻይና ቤጂንግ በተካሄደ የዘላቂ ልማት ግቦች ዓለም አቀፍ ስብሰባ በዘላቂ ልማት ግቦች ያላትን ተሞክሮ አጋርታለች።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ በቻይና ቤጂንግ በተካሄደው የዘላቂ ልማት ግቦች ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ተሳትፏል።
ስብስባው በዓለም አቀፉ የፓርላማ ሕብረት(IPU) እና በቻይናው ብሔራዊ የሕዝብ ኮንግረንስ(NPC) ትብብር የተዘጋጀ ነው።
ዶክተር ተስፋዬ በልጂጌ የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች አፈጻጸምና ምክር ቤቱ ለግቦቹ መሳካት እያደረገ ያለውን ድጋፍና ክትትል የተመለከተ ተሞክሮ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያም አሁን የጀመረችውን አመርቂ የለውጥ ጉዞ በማፋጠን ሕዝቦቿን ወደ ብልፅግና ለማድረስ እየሰራች እንደምትገኝ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በትክክለኛ የልማት ጎዳና ላይ ያለችና ለሌሎች ሀገራትም ልምድ መቅሰሚያ የምትሆን ሀገር ናት ብለዋል።
ይህን ጅምር በዘላቂነት ለማፅናት የሀገርን ሰላም፣ ክብር እና ብልጽግናን ማስጠበቅ የሁሉ አካል ኃላፊነት እንደሆነ መግባባት እንዲሁም በጋራ መቆምን የሚጠይቅ መሆኑን መግለጻቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ ለልማት ጉዞው ታሪካዊና ባህላዊ እሴቷን ጠብቃ ለትውልድ ማስተላለፍ የሚያስችሉ የልማትና ሌሎች ተግባራት ዕውን ማድረግ የቻለችውን ቻይና ልምድ መቅሰሟን ነው የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትሩ የገለጹት።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ(ዶ/ር) የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ከስብስባው ጎን ለጎን የቻይናን የለውጥና የልማት እንቅስቃሴዎች ጎብኝቷል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top