ትግራይን ለማዳን የሚደረገው ጥረት ያለ ችግኝ ተከላ ውጤት አይኖረውም፡- አቶ ጌታቸው ረዳ

4 Mons Ago 602
ትግራይን ለማዳን የሚደረገው ጥረት ያለ ችግኝ ተከላ ውጤት አይኖረውም፡- አቶ ጌታቸው ረዳ
ትግራይን ለማዳን የሚደረገው ጥረት ያለ ችግኝ ተከላ ውጤት አይኖረውም ሲሉ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አሥተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።
 
በትግራይ ክልል በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የማኖር መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመርሐ-ግብሩ ከክልል ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች እና የሕብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡
 
የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ በዚሁ ወቅት ባስተላላፉት መልዕክት፤ትግራይን ለማዳን የሚደረገው ጥረት ያለ ችግኝ ተከላ እዚህ ግባ የሚባል ውጤት አይኖረውም ብለዋል፡፡
 
በትግራይ ክልልን ዘላቂ ልማት ለማረጋገጥ ለተፈጥሮ ሐብት ዘርፍ ትኩረት በመስጠት መሥራት እንደሚገባም ገልፀዋል፡፡
 
ክልሉ በተፈጥሮ ሐብት ሥራዎች፣ ደንና አረንጓዴ ልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና አግኝቶ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጌታቸው፤ ይሁን እንጂ ባለፉት ዓመታት በሰው ሠራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የተፈጥሮ ሐብት ልማት ሥራው ወደ ኋላ መመለሱን ጠቅሰዋል፡፡
 
በተፈጥሮ ሐብቱ ያጋጠመው መራቆት መልሶ እንዲያገግም እና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የአረንጓዴ አሻራ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top