ለ40 ዓመታት የዘለቀ ችግኝ የመትከል ልምድ ያላቸው የሲዳማ ክልል ሸበዲኖ ወረዳ ነዋሪ አቶ ከምባታ ሀጢያ በአካባቢው ''የዝግባ አባት'' የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል።
ከቤተሰብ የወረሱት ችግኝ የመትከል ልምዳቸው ዛሬ በአካባቢያቸው ችግኝ በመትከል ዓርአያ እንዲሆኑ አድርጓል።
ችግኝ መትከል ምግብ ነው፤ እስትንፋስ ነው፤ በአጠቃላይ ዛፍ ህይወት ነው የሚል አቋም እንዳላቸውም ለኢቢሲ ተናግረዋል።
ችግኝ በመትከል ቤቴ እና ጓሮዬን በአትክልት እና ፍራፍሬ መሙላት ችያለሁም ብለዋል።
ለዘመናት ያለማንም ቀስቃሽ በሺዎች የሚቆጠር ችግኝ ተክያለሁ፤ አሁን ላይ የመንግስት አጀንዳ በመሆኑ እረፍት ተሰምቶኛል ይላሉ።
ነገ በሚካሄደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ ላይ አሻራችንን እናኑር የሚል ጥሪም አቅርበዋል።
በአስረሳው ወገሼ
#አረንጓዴዓሻራ
#GreenLegacy