በህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል የሁላችንም ርብርብ እና ቁርጠኝነት ያስፈልጋል - ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

4 Mons Ago 593
በህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል የሁላችንም ርብርብ እና ቁርጠኝነት ያስፈልጋል - ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)

በህጻናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል የፍትህ አካላትን ጠንካራ እርምጃ፣ የጤናና የትምህርት ሴክተሩን ርብርብ፣ የሃይማኖት አባቶችን ቁርጠኝነት እና አንቀሳቃሽነት ያስፈልጋል ሲሉ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

በብሔራዊ ጥምረት የሴት ልጅ ግርዛትና የልጅነት ጋብቻ በመከላከል ዙርያ ለተገኘው ውጤት የእውቅና መስጫ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

ያለእድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት ለማስቆም የተቋቋመው የጥምረቱ የስራ እንቅስቃሴ አምስተኛው ዓመት ላይ መድረሱን የተናገሩት ሚኒስትሯ፤ በተቀናጀ ጥረት በርካታ ህጻናትንና አፍላ ወጣት ሴቶችን ከአሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰትና ወንጀል መታደግ ተችሏል ብለዋል፡፡

ይህ ዘርፈ ብዙ ጥምረትና ስኬት ዓለም አቀፍ እውቅና ማግኘቱን በማስታወስ በቅንጅት መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግ የሚያረጋግጥ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ስር የሰደደው ማሕበራዊ ወግ፣ የተዛባ የስርዓተ ጾታ ግንኙነትና የተናጠል ጥረታችንና ቁርጠኝነታችን በሚፈለገው ደረጃ ከፍ ባለማለቱ የተነሳ ግን ልጆች አሁንም የጎጂ ልማዳዊ ድርጊትና የጥቃት ሰለባ ሆነው ቀጥለዋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመሆኑም ዛሬም የፍትህ አካላትን ጠንካራ እርምጃ፣ የጤናና የትምህርት ሴክተሩን ርብርብ፣ የሃይማኖት አባቶችን ቁርጠኝነት እና አንቀሳቃሽነት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

በአሸናፊ እንዳለ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top