በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው ዋነኛው የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ ነው፡- አቶ አህመድ ሽዴ

5 Mons Ago 703
በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው ዋነኛው የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ ነው፡- አቶ አህመድ ሽዴ
በተሟላ መልክ ወደ ትግበራ በገባው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ዋነኛው የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ ነው ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ገልጸዋል።
 
የገቢዎች ሚኒስቴር ከግብር ከፋዮች እና ባለድርሻ አካላት ጋር በታክስና በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ውይይት እያካሄደ ይገኛል።
 
በመድረኩ የተገኙት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የሀገር ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ባለፉት ሥድስት ዓመታት ተግባራዊ ሲደረግ መቆቱን ገልጸው፤ በዚህ በጀት ዓመት በተሟላ መልኩ ወደ ትግበራ ገብቷል ብለዋል።
 
በዚህም በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው በዋነኛነት የሀገር ውስጥ ገቢን በማሳደግ ሀገራዊ የልማት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ አቅም ማሳካት መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
 
ማሻሻያውን ተከትሎ ሊፈጠር የሚችለውን የኑሮ ጫና ለማቃለል፣በመንግሥት በኩል ቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ስለመሠራታውን ገልጸው፤ የሚፈጠሩ ጫናዎችም ጊዜያዊ ስለመሆናቸው ተናግረዋል።
 
የገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው፤ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራ ውስጥ የኢኮኖሚ ተንቀሳቃሽ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን አንስተዋል።
 
የገቢዎች ሚኒስቴር የሀገርን ገቢ አቅም ለማሳደግ የግብር ሥርዓትን ጠብቆ በተለየ ትኩረት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
 
በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር-2 ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከተመሠረተ ሁለተኛ ዓመቱ ሲሆን፤ በተመሠረተበት በመጀመሪያ ዓመቱ ብቻ ከ17 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማሰባሰብ መቻሉንም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።
 
በትዕግስቱ ቡቼ
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top