በክልሉ ብልሹ አሰራር ውስጥ የገቡ 196 አመራሮች ከኃላፊነት ተነስተዋል፡- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር

2 Mons Ago 391
በክልሉ ብልሹ አሰራር ውስጥ የገቡ 196 አመራሮች ከኃላፊነት ተነስተዋል፡- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልሹ አሰራር ውስጥ የገቡ 196 አመራሮች ከኃላፊነት መነሳታቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ።
 
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።
 
የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርትን ያቀረቡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፤ በመኸር እና በበልግ የግብርና ልማት 688 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ገልፀው፤በዚህም 19 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
 
በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦትና ሥርጭትም 190 ሺህ 13 ኩንታል መሆንኑን አንስተዋል።
 
በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ከ129 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸው ተገለጸ ሲሆን፤ በአንድ ጀንበር 20 ሚሊዮን 512 ሺህ 583 ችግኞች ተተክለዋል ብለዋል።
 
ርዕሰ መስተዳደሩ በሪፖርታቸው 54 ሺህ 795 ሜትሪክ ቶን የታጠበ እና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን ገልፀው፤ ከ70 ሺህ ቶን በላይ የማር ምርትም ማምረት መቻሉን ጠቁመዋል።
 
በሌማት ትሩፋት ውጤታማ ስራዎች ተከናወነዋል ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፤266 የወተት መንደሮች፣ 447 የዶሮ መንደሮች፣ 977 የንብ ሀብት መንደሮች እና 73 የዓሳ ግብርና መንደሮች መደራጀታቸውን ጠቅሰዋል።
 
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ ለ64 ሺህ ዜጎች ቋሚ የስራ ዕድል መፈጠሩን ርዕሰ መስተዳድሩ በሪፖርታቸው ገልጸዋል።
 
በሙሀመድ አልቃድር

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top