የኢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቻናል በቅርቡ ይመረቃል ******************

7 Days Ago
የኢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቻናል በቅርቡ ይመረቃል  ******************
የኢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቻናል በቅርቡ እንደሚመረቅ ተገልጿል፡፡
ኢቢሲ ቻናሉ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ውይይት በአፋን ኦሮሞ ከሚሰሩ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች ጋር አካሂዷል፡፡
ቻናሉ የይዘት ማሻሻያ በማድረግ እና አዳዲስ ፎርማቶችን በመጨመር የ24 ሰዓት ስርጭቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል፤ የኢቢሲ ምክትል ስራ አስፈፃሚ እና የቋንቋዎች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙክታር ሁሴን ተናግረዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ባለፉት 3 ዓመታት በለውጥ ላይ መሆኑን ያነሱት ኃላፊው ተቋሙ ለይዘት ከፍ ያለ ትኩረት መስጠቱን በ“ኢቢሲ ለጥበብ” የውይይት መድረክ ላይ ገልጸዋል፡፡
የኢቢሲ የአፋን አሮሞ ቻናል በቅርቡ በይፋ እንደሚመረቅም አስታውቀዋል፡፡
በተለያዩ ዘርፎች በአፋን ኦሮሞ እየሰሩ የሚገኙ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች በበኩላቸው፤ ከአዲሱ የኢቲቪ አፋን ኦሮሞ ቻናል ጋር በጋራ ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ በአፋን አሮሞ የ24 ሰዓት ስርጭት መጀመሩም ለኦሮሞ ጥበብ እና ቋንቋ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለብዝሃነት ትኩረት በመስጠት በባህር ዳር፣ በመቐለ፣ በሀረሪ፣ በሀዋሳ እና በመቱ ቅርጫፎችን ከፍቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በቅርቡም በሶዶ እና በጋምቤላ የክልል ቅርንጫፍ ለመክፍት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡
በላሉ ኢታላ
 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top