41 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው ተሰረዘ

10 Days Ago
41 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው ተሰረዘ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው ትምህርት የሚሰጡ እና የማይሰጡ የትምህርት ተቋማትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
 
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን መዝግበው የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶች 1332 የማስተማር ፈቃድ የተሰጣቸው ሲሆን 43 ት/ቤቶች በራሳቸው ጊዜ መቀጠል ስላልቻሉ ፈቃዳቸው መሰረዙን የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳኛው ገብሩ አብራርተዋል።
 
150 ት/ቤቶች ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያለ በመሆኑ ወደፊት የሚገለጽ መሆኑንን ገልፀዋል፡፡
 
41 ትምህርት ቤቶች የትምህርት ፖሊሲውን ባለመጠበቅና ስታንዳርዱን ባለማሟላታቸው ፍቃዳቸው የተሰረዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለ2017 ዓ.ም ትምህርት እንዳያስተምሩ የተከለከሉት ትምህርትቤቶች ምክንያት በትምህርት ፖሊሲ ጥሰት እና ስታንዳርድ ባለማሟላት መሆኑንም የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳኛው ገብሩ አብራርተዋል።
 
በተቋማቱ ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ሕጋዊ በሆኑ ት/ቤቶች ምርጫቸው ተጠብቆላቸው መማር እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
ማንኛውም የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ተቀብለው እንዲያስተምሩ እንዲሁም የተማሪዎችን መረጃ ያለምንም እንግልትና ቅድመ ሁኔታ እንዲሰጡ አሳስቧል።
 
የ2017 ዓ.ም የትምህርት ምዝገባ ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመርም አስታውቀዋል፡፡
 
በመሐሪ ዓለሙ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top