የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

13 ቀን በፊት
የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።

በክርስትና እምነት ተከታዮች ከሚከበሩት አበይት በዓላት መካከል የትንሳዔ በዓል አንዱ ሲሆን፤ በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ዕለት የሚታሰብበት ነው።

በዓሉ እግዚአብሄር አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅር በልጁ ሞትና ትንሳኤ የገለጠበት በመሆኑ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እጅግ ታላቅ በዓል ተደርጎ ይታያል።

በዓሉን በማስመልከት የተለያዩ የሀይማኖት መሪዎች ባስተላለፉት መልእክት፤ የትንሳኤ በአል እግዚአብሄር አምላክ ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅር በልጁ ሞትና ትንሳኤ የገለጠበት በመሆኑ፤ ምእመናንም፤ የተራቡትን በማብላትና፤ የተቸገሩትን በመርዳት ሊያከብሩት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ምዕመናን በዓሉን ሲያከብሩ ስለ ሀገር ሰላም እና እድገት እንዲያስቡ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የሀይማኖት መሪዎቹ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top