ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከጣሊያን የካራቢኔሪ ፓሊስ ምክትል አዛዥ ጀነራል ሪካርዶ ጋለኤታአ ጋር ተወያዩ

17 Days Ago
ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከጣሊያን የካራቢኔሪ ፓሊስ ምክትል አዛዥ ጀነራል ሪካርዶ ጋለኤታአ ጋር ተወያዩ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የጣሊያን የካራቢኔሪ ፓሊስ ምክትል አዛዥ ጀነራል ሪካርዶ ጋለኤታአን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
 
በውይይታቸውም፤ ከዚህ ቀደም በሮም ስምምነት በተደረሰባቸው ጉዳዮች አፈፃፀም እና ተጠናክረው በሚቀጥሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።
 
ጀነራል ሪካርዶ ጋለኤታአ የህዳሴ ግድብ ጥበቃን የሚያግዙ የፖሊስ ፓትሮል ጀልባዎችን በድጋፍ ለመስጠትና ሙያዊ እገዛ ለማድረግ፣ በፖሊስ አመራር፣ በፎሬንሲክ ሳይንስ እና በቪ.አይ.ፒ ጥበቃ ስልጠናዎችን በመስጠት አቅም ለመገንባት፣ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ እየተገነባ ላለው የፎሬንሲክ ሳይንስ ኢንስቲትዩትን በበቁሳቁስ ለማደራጀት ቃል ገብተዋል፡፡
 
በተጨማሪም የሁለቱ ሀገራት የፖሊስ ተቋማት የጋራ ስጋት የሆኑ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተለይ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን በተቀናጀና በትብብር ለመከላከል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
እ.ኤ.አ ጁላይ 2022 በኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራው ልዑካን ቡድን ወደ ጣሊያን ሮም ተጉዞ፤ ከጣሊያን ፖሊስ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር ጀነራል ቴኦ ሉዚ ጋር በደረሱበት ስምምነት መሠረት፤ ጀነራል ሪካርዶ ጋለኤታ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስን መጎብኘታቸው ተገልጿል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top