20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአቶ አህመድ ሽዴ መሪነት ተካሄደ

12 Days Ago
20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በአቶ አህመድ ሽዴ መሪነት ተካሄደ

20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ በወቅቱ የኢኒሼቲቩ ሊቀ መንበር የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ መሪነት በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተካሂዷል፡፡

ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና ዓለም ባንክ ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደው በዚህ መድረክ የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዝዳንትና የምስራቅ እና የደቡባዊ አፍሪካ ሃላፊ ቪክቶሪያ ክዋክዋ እንዲሁም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

በስብሰባው የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ሚኒስትሮች፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ ተወካዮች፣ የአረብ ባንክ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት፣ የሳዑዲ ልማት ፈንድ፣ የአሜሪካ እና የጃፓን ልዩ መልዕክተኛ ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አቶ አህመድ ሽዴ፤ ወደ ትግበራው ከገባ አምስት አመታትን ያስቆጠረው ኢኒሼቲቩ የሀብት ማሰባሰብ ስውራ ስኬታማ መሆኑን ገልጸው፤ ጥረቶቹን የበለጠ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በስብሰባው የተሳተፉት ድርጅትና ተቋማት ኢኒሼቲቩ ባዘጋጀው ህጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ በመደበኛነት አጋር ሆነው እንዲቀጠሉም ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በፈረንጆቹ 2019 ማብቂያ በአፍሪካ ቀንድ የፋይናንስ ሚኒስትሮች የተቋቋመው ኢኒሼቲቩ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ሶማሊያን፣ ጂቡቲን፣ ኤርትራን፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን በአባልነት ያቀፈ ነው፡፡

በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ የዓለም ባንክ እና አውሮፓ ሕብረት ድጋፍ የተቋቋመው ኢኒሼቲቩ ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር እንዲሁም በልማት ስራዎች በተለይም በመሰረተ ልማት፣ ንግድ፣ አቅም ግንባታ መስኮች የተሻሉ ውጤቶችን ማምጣት ዋነኛ የትኩረት አጀንዳ አድርጎ ይሰራል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top