ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተረከበች

28 Days Ago
ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተረከበች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት የተበረከተላትን የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተረክባለች።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂሮኖሪ ሽልማቱን ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ አስረክበዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ፤ በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል በስፖርት ዲፕሎማሲና ልውውጥ ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ፣ በሌሎች ሀገራት እና አካባቢዎች መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ፣ ለአትሌቲክስ እድገት፣ ለሀገር ሰላም ላበረከተችው አስተዋፅኦ ነው ዕውቅና የተሰጣት።

ይህ ዕውቅና እና ሽልማት እኤአ ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሀገር ዜጎች በጃፓን መንግስት የሚሰጥ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top