የመቻል ስፖርት ክለብ በቀጣይ 5 አመታት ስታዲየም እንደሚገነባ አስታወቀ

9 Mons Ago 889
የመቻል ስፖርት ክለብ በቀጣይ 5 አመታት ስታዲየም እንደሚገነባ አስታወቀ

የመቻል ስፖርት ክለብ በቀጣይ አምስት አመታት ስታዲየም እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሚሆነውን የስፖርት ህክምና ማእከል እንደሚገነባ አስታውቋል።

የመቻል ስፖርት ክለብ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር ሰይፈ ጌታሁን በሰጡት መግለጫ ቦርዱ ላለፉት ሰባት ወራት ጠንካራ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ የቦርድ አመራሩ እንዲቋቋም የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ላቅ ያለ ሚና አንደነበራቸው አንስተዋል።

መቻል በቀጣይ አምስት አመታት ከነበረበት በእጥፍ በውጤት ይሁን በኢኮኖሚ ለማጎልበት በሁሉም የስፖርት ዘርፍ ይሰራልም ብለዋል።

አዲሱ አመራር ከዚ በበለጠ ስኬታማ ለመሆን ሰፋፊ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ እና በቀጣይ ከተፎካካሪነት ባለፈ በተደጋጋሚ ዋንጫ ለማንሳት እንደሚሰራም ጠቁመዋል።

አዲሱ የቦርድ አመራር ወደ አመራርነት ከመጣበት ወራት ጀምሮ ወደ ተግባር የገባባቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች መኖራቸውን የጠቀሱት የቦርድ ሰብሳቢው፤ በተለይም ደግሞ ባለሀብቶችን ወደ ስፖርቱ በማምጣት እየተሰራ ያለው ስራ በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ ዓመታትም የስታዲየም ግንባታ፣ ትልልቅ ዋንጫዎችን ማሳካት፣ በአፍሪካ ተሳታፊ መሆን እና የሴት ቡድን በሌላቸው የተለያዩ ስፖርቶች ላይ የሴት ቡድን ማቋቋም ክለቡ እቅዶ እየሰራባቸው መሆኑን የቦርድ ሰብሳቢው ገልጸዋል። 

የመቻል ስፖርት ክለብ ወቅታዊ ሁኔታ እና የክለቡን ቀጣይ ዕቅድ በተመለከተ በክለቡ የሥራ አመራር ቦርድ መግለጫ በተሰጠበት ወቀት፤ ስፖርት ክለቡ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች ያስመዘገባቸው ስኬቶች ያረፈበትን ሙዚየም እንዲሁም ጂምኒዚየሙን አስጎብኝቷል።

በምህረት ተስፋየ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top