"ስለ እናት ምድር" የተሰኘ በሀገር ፍቅርና ሰራዊቱ ህይወት ላይ ያተኮረ ፊልም ተመረቀ

9 Mons Ago 1267
"ስለ እናት ምድር" የተሰኘ በሀገር ፍቅርና ሰራዊቱ ህይወት ላይ ያተኮረ ፊልም ተመረቀ

"ስለ እናት ምድር" የተሰኘ በሀገር ፍቅር እና በመከላከያ ሰራዊት ህይወት ላይ ያተኮረ ፊልም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ተመርቋል።

በፊልሙ ምርቃት ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ፣ የመከላከያ ሰራዊት አመራርና አባላት፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ዲፕሎማቶች፣ የኪነ-ጥበብ ሰዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዚሁ ወቅት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ ኢትዮጵያ ሁልጊዜ ታሪክ ብትሰራም ታሪኩን ከትውልድ ወደ ትውልድ በመፅሀፍ እና ኪነ ጥበብ ስራዎች ቀርፆ ማስተላለፍ ላይ አለመሰራቱን ገልፀዋል።

በዚህ ረገድ መከላከያ ሰራዊቱ እየፈፀማቸው ያሉትን ታሪካዊ ስራዎች በመፅሀፍ እና በኪነ-ጥበብ ስራዎች ለትውልድ የማስቀመጥ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዛሬው ዕለት በሰራዊቱ አገር ፍቅርና ተጋድሎ ላይ የተሰራው ፊልም የዚሁ አካል መሆኑን ነው ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የገለፁት።

ፊልሙን ያዘጋጀው አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ በበኩሉ፤ አገርን ባለን ተስጦ እና መክሊት ማገልገል ይገባል ሲል ገልጿል።

በአርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ የተዘጋጀውና አስራ ስምንት ወራትን የፈጀው ፊልሙ ከ30 ሺህ ሰው በላይ ተሳትፎበታል።

በሙሉ ግርማይ

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top