በቀጠናው የተሰማራው ክፍለጦር አዛዥ ኮሎኔል አለሜ ታደለ እንደተናገሩት፤ ክፍለ ጦሩ ከአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ጋር በጎንጂ ቆለላ ባደረገው ኦፕሬሽን ጽንፈኛው ሲጠቀምባቸው የነበሩ 20 ወታደራዊ የግንኙነት ሬድዮ ከነ ቻርጀሩ ተማርኳል።
በስምሪቱ ሰባት የጽንፈኛዉ አባላት መደምሰሳቸው እና ዘጠኙ መማረካቸው የተገለፀ ሲሆን፤ መሳሪያ እንዲገዙ የተላኩ የቡድኑ ሁለት አባላትም መያዛቸዉም ተጠቁሟል።
ጽንፈኛው ከሕብረተሰቡ የዘረፈው ሁለት ቡና የጫነ አይሱዙ ኦባማ ከነ አጋቾቹ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቅሷል።
የጥፋት ቡድኑ ለማምለጥ ሲበርበት የተገለበጠ አንድ አውቶቡስ፣ አምስት ሞተር ሳይክል፣ ከማኅበረሰቡ የዘረፈው 20 ጀሪካን ነዳጅ እና ስድስት ኩንታል በርበሬ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ከሃገር መከላከያ ሠራዊት ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።