የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ማኀበረሰብ በተለይም ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች በሀገራችን ኢኮኖሚ የሚጫወቱት ሚና ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልእክት፤ "ዛሬ ጠዋት ከነዚህ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ጋር በጠቃሚ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል" ብለዋል።