ወጣቶች ከዓድዋ ድል በመማር ለሀገራቸው ልማት እና ዘላቂ ሰላም ተግተው ሊሰሩ ይገባል ተባለ

10 Mons Ago 839
ወጣቶች ከዓድዋ ድል በመማር ለሀገራቸው ልማት እና ዘላቂ ሰላም ተግተው ሊሰሩ ይገባል ተባለ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል "ዓድዋን ለዘላቂ ሰላም እና ጠንካራ ሀገረ-መንግስት" በሚል መሪ ሀሳብ የወጣቶች የውይይት መድረክ፤ በክልል ሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ የወጣቶች ቢሮ እና በክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ  አዘጋጅነት እየተካሄደ ነው፡፡

በወጣቶቹ  የወይይት መድረክ ላይ የተገኙት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ የወጣቶች ዘርፍ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ እናትነሽ ማሩ፤  የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን ሀገራዊ ፍቅር፣ አንድነት እና ጽናትን ያሳየ ሀገራዊ ድል በመሆኑ ለአሁኑ ትውልድ አስተማሪነቱ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የዚህ ዘመን ወጣቶችም ከዓድዋ ድል በመማር ለሀገራቸው ልማት ሰላም እና አብሮነት በሀገር ፍቅር ስሜት ሊሰሩ እንደሚገባ ወ/ሮ እናትነሽ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በወይይቱ የተገኙት ወጣቶችም እንደሀገር የተጀመሩ የሰላም፣ የልማትና የመልካም እስተዳደር ስራዎች ወጤታማ አንድሆኑ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት የዓድዋን ድል እንደግማለን ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

በጀማል አህመድ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top