የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ተወያየ

5 Mons Ago
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ከጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ተወያየ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈፃፀም መርማሪ ቦርዱ በአማራ ክልል የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘሙን ተከትሎ በቀጣይ በሚከሆኑ ተግባራት ዙሪያ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱም፤ ባለፉት ጊዜያት ለዕዙ የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች አፈፃፀም፣ አዋጁ ከተራዘመ በኋላ ያለው አሁናዊ ክልላዊ ሁኔታ በተለይም ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶች እንዳይፈፀሙ ከመከላከል አኳያ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ምክክር ተደርጓል፡፡

ክልሉን ወደ ሠላማዊ ሁኔታ ለማሸጋገር የተሠራው ሥራ አንፃራዊ ሠላም ማስገኘቱ እና ሠላሙን ለማፅናት አሁንም ቀሪ ሥራዎች መኖራቸው ተጠቅሷል፡፡

ቦርዱ ባለፉት ስድስት ወራት ወደ ክልሉ በማቅናት ክትትል ማድረጉን በውይይቱ ላይ ማንሳቱን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

ጠቅላይ መምሪያ ዕዙ በበኩሉ፤ በክልሉ የተመዘገቡና እየተመዘገቡ ያሉ የሠላም ጉዳዮችን፣ ከዚህ በፊት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦች የተፈፀሙትንና እየተፈፀሙ ያሉትን ጉዳዮች እንዲሁም መፈፀም ያለባቸው ተግባራትን በዝርዝር አቅርቧል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top