የወገብ ህመም እንዴት ይከሰታል?

7 Mons Ago 1630
የወገብ ህመም  እንዴት ይከሰታል?

 

አን ላይ በተደጋጋሚ ወገቤን አመመኝ የሚሉ ሰዎች በስፋት ይሰማሉ፡፡ ይህ የወገብ ህመም ከእድሜ መግፋት እና ከወሊድ ጋር ቢያያዝም በወጣቶች ላይም ይከሰታል፡፡

 

የወገብ ህመም ሲባል በጀርባ በኩል ያለውን የታችኛውን የአካል ክፍል ወይም ወደ መቀመጫ አከባቢ ያለውን የህመም ስሜት የሚያመለክት ነው፡፡ የወገብ ህመም ምንም አይነት ስራዎችን ስንሰራ ከሚፈጥረው ቀላል የህመም ስሜት ጀምሮ ፣ እየተባባሰ ሲሄድ በእግራችን ጉዞ ማድረግ እንዳንችል እና ፓራላይዝ የማድረግ ደረጃም ላይ ሊያደርስ ይችላል::

  

 የወገብ ህመም ምልክቶች

 

  • ትኩሳት
  • የእግር መደንዘዝ ወይንም መስነፍ
  • ሽንትና ሰገራ የመቆጣጠር ችግር
  • ከዚህ በፊት የአጥንት መሳሳት
  • ህመሙ በጣም እየባሰ መሄድና በእረፍት ወይንም በአቀማመጥ የማይሻል ከሆነ
  • ህመሙ በሳምንት ውስጥ ለውጥ ከሌለው አና ተመሳሳይ ስሜቶች ሲኖሩ

 

 የወገብ ህመም መንስኤዉ ምንድነዉ?

 

  • የወገብ አጥንት መዛነፍ
  • የመገጣጠሚያ አካባቢዎች መቆጣት
  • የአጥንት መብቀል
  • የተለያዩ ኢንፌክሽኖች (የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን፣ የማህፀን ኢንፌክሽን)
  • አደጋ (መደብደብ፤ ምት ወዘተ)
  • ከመጠን ያለፈ ውፍረት
  • እግርን አጣምሮ መቀመጥ፡-የዳሌ ጡንቻ እንዲወጣጠር ስለሚያደርግ ህመም ይፈጥራል
  • ለብዙ ሰዓት መቆም
  • ሲጋራ ማጨስ፡- ሲጋራ በውስጡ ኒኮቲን ስላለው በቂ ሆነ ደም ዝውውር እንዳይዳረስ ስለሚያደርግ

 

 

የወገብ ህመም መፍትሄ እና ህክምና

 

  • የእንቅሳቃሴ ህክምና (ፊዚዮቴራፒ) በማድረግ ማስተካከል ይቻላል፡፡

 

  • ከዚህ ሌላ ደግሞ የካይሮፕራክቲክ ህክምና እንዲሁም አኮፓንቸር ህክምና ደግሞ ውጤታማ ናቸው፡፡

 

  • በተቻለ መጠን መንቀሳቀስ ምክንያቱም እንቅስቃሴ በተደረገ ቁጥር የወገብ ህመም የመሻል እድሉ እየጨመረ ይሄዳል፡፡

 

የሚታዘዙ የመፍትሄ እርምጃዎችን/ ህክምናዎችን ተግባራዊ ማድረግ ለምሳሌ፦

 

* የፊዚዮቴራፒ ህክምና

* የመድሀኒት ህክምና

* የቀዶ ጥገና ህክምና

* የፊዚዮቴራፒ ህክምና: በአብዛኛው የወገብ ህመም ዋና መፍትሄዉ የፊዚዮቴራፒ ህክምና ነው።

 

ፊዚዮቴራፒ ሲባል በአብዛኛው ማህበረሰባችን ዘንድ የሰውነት ማሳጅ እንደሆነ ይታሰባል።

 

ነገር ግን ፊዚዮቴራፒ የሰውነት ማሳጅ ሳይሆን በውስጡ ብዙ የህክምና ሳይንስ እና ቴክኒክ የያዘ በሙያው እውቀት ባላቸው እና በሰለጠኑ ስፔሻሊስቶች ወይም ኤክስፐርቶች ብቻ የሚሰጥ የህክምና ሳይንስ ነው፡፡ በመሆኑም በህክምና የሚሰጡ የሀኪም ትዛዝን በመከት ከህመሙ መፈወስ ይቻላል፡፡

 

በሜሮን ንብረት


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top