በሐሰተኛ ሰነድ አጭበርብሮ ከባለሃብት 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሰወረው ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ የተባለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ልዩ ቦታ ሴንትራል ማተሚያ ቤት አካባቢ በሐሰተኛ ሠነድ አጭበርብሮ ከባለሀብቱ 13 ሚሊዮን 888 ሺህ ብር ተቀብሎ የተሠወረውን ቱጁባ ቶልቻ ሰንበታ የተባለውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዚህ ግለሰብ ተታለልኩ ወይም ተጭበረበኩ የሚል ማንኛውም ሰው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ቢሮ ቀርቦ ሪፖርት እንዲያደርግ ተቋሙ ያስታውቃል።
ኅብረተሰቡ በተመሳሳይ የወንጀል ተግባር እንዳይታለል ራሱን እንዲጠብቅና በወንጀል መከላከል ውስጥ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።