የሰላም ሚኒስቴር ከሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ መስራ በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ

9 Mons Ago 510
የሰላም ሚኒስቴር ከሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ መስራ በሚችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ
የሰላም ሚኒስቴር ከተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች ሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ ጋር በሰላም ግንባታ ሂደት ዙሪያ በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቷል።
 
የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ፤ የሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር የሆኑትን ዶ/ር ኸሊፋ ሙባረክን እና የልዑካን ቡድናቸውን በዛሬው ዕለት ተቀብለው አነጋግረዋል።
 
በውይይቱ ሚኒስትር ድኤታው፤ የሰላም ሚኒስቴር ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና ብሔራዊ መግባባትን ለማጎልበት እያከናወናቸው ስለሚገኙ ተግባራ ለልዑካን ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል።
 
በሃገሪቱ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት እና የሃገረ መንግስት ግንባታ ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወን ሚኒስቴሩ የተለያዩ አካላትን በማስተባበ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
 
የሰላም ባህሪ ዓለም አቀፋዊ ገፅታ ያለው በመሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ዴዔታው፤ ከተለያዩ ሃገራት የጥናት እና ምርምር ተቋማት ጋር ተባብሮ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
 
ለኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆነችው የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የትምህርት ተቋማት ጋር የሚደረገው ትብብርም ዘርፈ ብዙ ትርጉ እንዳለውም ገልፀዋል።
 
የሞሃመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርስቲ ቻንስለር ዶ/ር ኸሊፋ ሙባረክ በበኩላቸው፤ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ የተለያዩ ልምዶችን እንደምትወስድ በመግለጽ፤ሚኒስቴሩ ለሚያከናውናቸው የሰላም ግንባታ ተግባራት ድጋፍ ለማድረግ ዩኒቨርስቲው በትብብር እንደሚሰራ ተናግረዋል።
 
ዩኒቨርስቲው በሰላም ግንባታ ዙሪያ ከሚኒስቴሩ ጋር በትብብር ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ቻንስለሩ መግለጻቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top