ትኩረት የተነፈገው ኤች አይ ቪ/ኤድስ

1 Yr Ago 587
ትኩረት የተነፈገው ኤች አይ ቪ/ኤድስ

በዓለማችን እስካሁን ድረስ ከ40 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተያዙ ሲሆን ስርጭቱ በሁሉም ሀገራት በመቀጠሉ ዋነኛው የዓለም የህዝብ ጤና ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል።

እ.ኤ.አ. በ2022 መጨረሻ የዓለም ጤና ድርጅት ባጠናው ጥናት መሰረት 39 ሚሊዮን ሰዎች ከኤች አይቪ ቫይረስ ጋር ይኖራሉ ተብሎ ይገመታል፤ ከእነዚህ ውስጥ 25.6 ሚሊዮን የሚሆኑት አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ እንደሆነም ተነግሯል ።

በኢትዮጵያ 622 ሺህ ሰዎች የኤች አይቪ/ኤድስ ቫይረስ በደማቸው እንደሚገኝ ይገለጻል።

በሀገሪቱ በየዓመቱ ከ11 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች በኤች አይቪ ቫይረስ እንደሚያዙ የፌደራል ኤች አይቪ /ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል ፡፡

እንደ ጽህፈት ቤቱ መረጃ አዲስ ከሚያዙት ውስጥ 67 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች ናቸው።

በኢትዮጵያ አሁን ላይ በከፍተኛ  ቁጥር ስርጭቱ እየጨመረ ቢሆንም፤   በዜጎች ላይ እታየ ያለው ከፍተኛ  መዘናጋት ምክንያት ስርጭቱ እየተስፋፋ እንደሆነም ያገኘናቸው መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ጋምቤላ፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ አፋር፣ ትግራይ፣ አማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ  ደረጃ የሚታይባቸው እንደሆነ ይጠቀሳል።

ኤች አይ ቪ ቫይረስ ነጭ የደም ሴሎችን በማጥቃት የሰውነት በሽታን የመከላከል ስርዓትን የሚያዳክም ነው፡፡

ይህም እንደ ሳንባ ነቀርሳ፣ ኢንፌክሽኖች እና አንዳንድ ነቀርሳዎች ሰዎች በቀላሉ እንዲጠቁ ያደርጋቸዋል።

ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት በማድረግ እና በደም ንክኪ በሽታው ሊተላለፍ ይችላል።

ቫይረሱ የለባት እመጫት የጡት ወተት ካጠባች ቫይረሱን ሊተላለፍ ይችላል።

ሰዎች ኤች አይ ቪ ቫይረስ እንዳይያዙ ተገቢውን ትኩረት እና ጥንቃቄዎች ሊደረጉ እንደሚገባ የጤና ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡

በሜሮን ንብረት

 


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top