የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ከዩክሬን ጋር ባለው ጦርነት መጪውን የትንሣኤ በዓል አስመልክተው ተኩስ አቁም አወጁ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቅዳሜ ከሌሊቱ 6 ሰዓት ላይ የሚጀምረውን እና እስከ እሁድ እኩለ ሌሊት የሚዘልቅ የተናጠል ተኩስ አቁም ማወጃቸውን ነው የክሬምሊን ምንጮች የገለጹት።
ዩክሬንም ይህን ተከትላ ለትንሣኤ በዓል ሙሉ ተኩስ አቁም ታደርጋለች ብለው እንደሚጠበቅ የአልጄዚራ ዘገባ ያመላክታል።
ሩሲያ ባወጀችው የተኩስ አቁም የትንሳኤ በዓል እስኪያልፍ ሁሉንም ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እንደምታቆም ተነግሯል፡፡