ኢቢሲ የሚያስተላልፈው ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ዛሬ ይካሄዳል

18 Hrs Ago 142
ኢቢሲ የሚያስተላልፈው ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ ዛሬ ይካሄዳል

ኢቢሲ የሚያስተላልፈው ተጠባቂው ቲክቶክ ክሬቲቭ አዋርድ በዛሬው ዕለት በድምቀት ይካሄዳል፡፡

የሽልማት መርሐ-ግብሩ በኢቢሲ ዶትስትሪም እና በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል በቀጥታ ስርጭት ለሚሊዮኖች ይደርሳል፡፡

በውድድሩ ከ300 በላይ በጎ ተፅዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች በ24 ዘርፎች ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

የቲክቶክ እድምተኛ ከሆኑ በቀሪ ሰዓታት ለሚወዱት እና ለሚያደንቁት ቲክቶከር ድምጽዎን መስጠት ይችላሉ፡፡

ቲክቶክ ላይ ምን አይነት ይዘቶችን አዘውትረው ይመለከታሉ፤ ለእርስዎ በየዘርፉ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮችስ እነማን ናቸው?

ዓለም ላይ ከ1 ቢሊዮን በላይ ተጠቃሚ ያለው ቲክቶክ በሰዎች አስተሳሰብ እና ስብዕና ላይ ብርቱ አሻራ እያሳረፈ እንደሚገኝ አያጠያይቅም፡፡

ቲክቶክ ላይ በኃላፊነት ስሜት የመዝናኛ፣ ትምህርታዊ እና ሌሎች ይዘቶችን በመስራት በጎ ተጽዕኖ የፈጠረብዎ ቲክቶከር ማን ነው?

ብዙዎች የበጎ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ፈለግ እንዲከተሉ አይተው ለማይጠግቡት፣ በጨዋነት ለሚያዝናናዎት እንዲሁም በዕውቀት ለሚያስተምርዎት ቲክቶከር ድምጽዎን ይስጡ፡፡

እነሆ ማስፈንጠሪያው

https://www.tiktokcreativeawards.com/


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top