በ2024 የዱባይ ግሎባል ሶከር አዋርድ ሪያል ማድሪድ አብዛኛውን ሽልማት አሸነፈ

16 Hrs Ago 98
በ2024 የዱባይ ግሎባል ሶከር አዋርድ ሪያል ማድሪድ አብዛኛውን ሽልማት አሸነፈ

በዱባይ ስፖርት ምክር ቤት በየዓመቱ የሚዘጋጀው ግሎባል ሶከር አዋርድ የዘንድሮው ሽልማት ሪያል ማድሪድ እና የክለቡ ተጫዋቾች እና አመራሮች አብዛኛውን ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

የሽልማት ስነ-ስርዓቱ ትናንት በዱባይ ለ14ኛ ጊዜ ሲካሄድ፤ ሪያል ማድሪድ የዓመቱ የዓለም ምርጥ ቡድን ሽልማትን አሸንፏል።

ብራዚላዊ የሪያል ማድሪድ ተጫዋች ቪኒሺየስ ጁኒየር የዓመቱ የዓለም ምርጥ ተጫዋች ሲባል፤ የሪያል ማድሪዱ ግብ ጠባቂ ቲቦ ኮርቶዋ የዓመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በሚል ተሸልሟል፡፡

እንግሊዛዊ የሪያል ማድሪድ አማካይ ጁድ ቤሊንገሃም የዓመቱ ምርጥ አማካይ ተጫዋች ተብሎ ተሸልሟል።

የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የዓመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ሽልማትን ሲወስዱ፤ የክለቡ ፕሬዝዳንት ፍሎሬንቶ ፔሬዝ ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ፕሬዚዳንት ተብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዓመቱ በመካከለኛው ምስራቅ ምርጥ ተጫዋች ክብርን  ከግሎባል ሶከር አግኝቷል።

የባርሰሎና የክንፍ ተጫዋች ላሚን ያማል የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።

በላሉ ኢታላ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top