አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

2 Mons Ago 433
አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢዮርግ ሳንጃር ጋር ተወያዩ። 

ተወያዮቹ በኢትዮጵያ እና በኖርዌይ መካከል ስላለው ጠንካራ አጋርነት በተለይም በትምህርት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በሰላምና ደህንነት ዙሪያ አተኩረው ሃሳብ ተለዋውጠዋል። 

የሁለቱን ሀገራት ትብብር የበለጠ ማስፋት እንደሚያስፈልግ አምባሳደር ምስጋኑ ገልጸዋል። 

አክለውም የኖርዌይ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። 

ቢዮርግ ሳንጃር በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በቀጣናው መረጋጋት ላላት ሚና ኖርዌይ አድናቆት እንዳላት ገልጸዋል። 

ሁለቱ ወገኖች በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በውሃ ሃብትና በጤና ላይ ትብብርን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። 

በተጨማሪም በሁለትዮሽ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ መወያታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top