ኢቢሲ ታላቁ የሰላም ሩጫን በሚዲያ አማራጮቹ ለዓለም በቀጥታ ስርጭት በማድረሱ የዋንጫ እውቅና ተበረከተለት

3 Mons Ago 352
ኢቢሲ ታላቁ የሰላም ሩጫን በሚዲያ አማራጮቹ ለዓለም በቀጥታ ስርጭት በማድረሱ የዋንጫ እውቅና ተበረከተለት

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን "ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀውን ታላቁ የሰላም ሩጫን በሁሉም የሚዲያ አማራጮቹ ለዓለም በቀጥታ ስርጭት በማድረሱ የዋንጫ እውቅና ተበርክቶለታል፡፡   

ከሰላም ሚኒስቴር የተበረከተውን የዋንጫ እውቅና የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በቦታው ተገኝተው ከሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም እጅ ተቀብለዋል፡፡

ኢቢሲ ታላቁ የሰላም ሩጫ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ ሁነቱን በቅርበት በመከታተል ለአድማጭ ተመልካች በማድረስ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህም ታላቁ የሰላም ሩጫ በሀገራችን ብሎም በመላው ዓለም እንዲተላለፍና አድማጭ ተመልካች ጋር እንዲደርስ ኮርፖሬሽኑ ትልቅ ሚና በማበርከቱ ከሩጫው አስተባባሪዎች ምስጋና ተችሮታል፡፡

በመርሃ ግብሩ የመከላከያ ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ለታላቁ የሰላም ሩጫ እገዛ ያበረከቱ መሰል ተቋማት እውቅና ከተሰተጣቸው መካከል ናቸው፡፡

"ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም" በሚል መሪ ሀሳብ በሰላም ሚኒስቴር የተዘጋጀው ታላቁ የሰላም ሩጫ አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች፣ ዞኖች፣ ከተሞች እና ወረዳዎች ተካሂዷል፡፡


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top