በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የካንሰር ህክምና ማዕከል ተመረቀ

13 Days Ago
በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የካንሰር ህክምና ማዕከል ተመረቀ

በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የካንሰር ህክምና ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች የህክምና አገልግሎቶች መስጫ ማዕከላት ተመረቁ ።

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ፣ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር በየነ በራሳ እንዲሁም የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አያኖ በራሳ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ማዕከሉ በዛሬው እለት ተመርቋል።

የካንሰር ጨረራ ህክምና ማዕከል ፤ የፎረንሲክ እና ስነ _ምረዛ ክትትል፣ሞዴል ፋርማሲ ፣ የስነ -አዕምሮ ህክምና፣የጨቅላ ህፃናት እንዲሁም የፅኑ ህክምና አገልግሎት መስጫን ያካተተ ነው።

የካንሰር ጨረራ ህክምና ማዕከሉ ከጅማ፣ሀረር እና አዲስ አበባ በመቀጠል በሀገሪቱ አራተኛው ሲሆን ከመላ ሃገሪቱ በሪፈር የሚመጡ የካንሰር ታማሚዎችን ተቀብሎ ህክምና እንደሚሰጥም ተገልጿል ፡፡

በሚካኤል ገዙ


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top