በኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራ ልዑክ በእንግሊዝ ሀገር የስራ ጉብኝት አደረገ

7 Mons Ago
በኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የተመራ ልዑክ በእንግሊዝ ሀገር የስራ ጉብኝት አደረገ

የልዑኩ አባላት በጉብኝታቸው መቀመጫውን በለንደን ከተማ ባደረገውን የዩናይትድ ኪንግደም የብሔራዊ ወንጀል ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ዙሪያ ከኤጀንሲው አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያን ተሞክሮ ያጋሩ ሲሆን፤ በዚህም በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ አቅምን በማሳደግ የተመዘገቡት አመርቂ ውጤቶችን አብራርተዋል።

ሁለቱ ወገኖች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በተለይም ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ ለመመርመር እ.ኤ.አ በሴፕቴምበር 26 ቀን 2023 በአዲስ አበባ ተመርቆ የተከፈተውን የሬድ ፎክስ ማዕከል በማጠናከርና በማስፋፋት ዙሪያም ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

የማዕከሉን አቅም ለማሳደግ በቴክኖሎጂ፣ በስልጠና እንዲሁም በግብዓት ድጋፍ ለማድረግ የብሔራዊ ወንጀል ኤጀንሲ ዳይሬክተር ጄነራል ለኦፕሬሽን ዴቪድ ሀከር ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።

ለኢትዮጵያ ፖሊስ አመራሮችና አባላት በእንግሊዝ ሀገር የትምህርት እድል ለመስጠትም ተስማምተዋል።

በተጨማሪም፥ የልዑካን ቡድኑ የዩናይትድ ኪንግደም የብሔራዊ ወንጀል ኤጀንሲ የፖሊስ ክትትል ቡድን የሚጠቀምባቸውን ትጥቆች መጎብኘቱን ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top