የዘንድሮው ‘COP28’ ኢትዮጵያ ያላትን ቱባ ባህል፣ ታሪክና ተፈጥሮ ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅም ምቹ መደላድል ፈጥሯል - ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

7 Mons Ago
የዘንድሮው ‘COP28’ ኢትዮጵያ ያላትን ቱባ ባህል፣ ታሪክና ተፈጥሮ ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅም ምቹ መደላድል ፈጥሯል - ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

የዘንድሮው የ‘COP28’ ጉባዔ ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች እያከናወነችው ያለውን ልማት በበቂ ሁኔታ ለማስተዋወቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑን የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ገለጹ።

በመድረኩ ኢትዮጵያ የራሷ በሆነ ሰፊ የማሳያ ቦታ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራችው ያለውን ጠንካራ ስራ ለማሳየት መቻሏንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

መድረኩ ኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የሰራቻቸውን ስራዎች ለማሳየት ዕድል የፈጠረላት መሆኑን አብራርተዋል።

በዋናነት የዘንድሮውን ‘COP28’ ለየት የሚያደርገው ኢትዮጵያ ሰፊ የሚባል የኤግዚቢሽን ቦታ በማዘጋጀት ያላትን ለማስተዋወቅ የተሞከረበት በመሆኑ ነው ብለዋል።

አውደ ርዕዩ ኢትዮጵያ ያላትን ቱባ ባህል፣ ታሪክ እና ተፈጥሮ ለተቀረው ዓለም ለማስተዋወቅም ምቹ መደላድል የፈጠረላት መሆኑን ዶ/ር ፍጹም አሰፋ ገልጸዋል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top