ኢትዮጵያን ጨምሮ 20 ሀገራትና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

1 Yr Ago
ኢትዮጵያን ጨምሮ 20 ሀገራትና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅቶች ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በጋራ ለመከላከል ተስማሙ

በጣሊያን ጋባዥነት በሮም በተካሄደው ዓለም አቀፉ የልማት እና የፍልሰት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ 20 ሀገራት ተሳትፈዋል። 

በጉባኤው ህገወጥ ፍልሰትን ለመከላከል እና ከምንጩ ለማስቀረት የሚያስችል ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ ያለመ ውይይት ተካሂዷል። 

ይህን ተከትሎም ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ ኢስላማዊ የልማት ባንክ እና የዓለም ባንክን ጨምሮ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና ተሳታፊ ሀገራት ‘Rome Process’ የተሰኘ ስምምነት አድርገዋል። 

ይህ የሮም ኢኒሸቲቭ እንደአስፈላጊነቱ በየጊዜው ተገናኝቶ የጋራ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል ስልታዊ፣ ሁሉን አቀፍና አካታች መድረክ ነው ተብሎለታል። 

ስምምነቱ በሜዲተራኒያን ዳርቻ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና አፍራካ የሚያጋጥም አስገዳጅ ፍልሰትን እና ህገውጥ የሰዎች ዝውውርን ከምንጩ ለመከላከካል ያስላችልም ተብሏል። 

ይህንን ዓላማ ለማሳካት ተሳታፊ ሀገራቱ እና ዓለም አቀፍ አጋር ድርጅቶቹ በማህበራዊ ዋስትና፣ በኢኮኖሚ ልማት፣ በድህነት ቅነሳ፣ በስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎትን ማሳደግ እንዲሁም በትምህርት ጥራት ላይ ትኩረት ለማድረግ መስማማታቸውን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል። 

የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት ኢትዮጵያ፣ አልጄሪያ፣ ባህሬን፣ ግብፅ፣ ግሪክ፣ ዮርዳኖስ፣ ኩዌት፣ ሊባኖስ፣ ሊቢያ፣ ማልታ፣ ሞሪታኒያ፣ ሞሮኮ፣ ኒጀር፣ ኳታር፣ ኦማን፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ስፔን፣ ቱኒዚያ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች እና የግሪክ ቆጵሮስ አስተዳደር ናቸው።


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top