አትሌት ብርቄ ኃየሎም በሴቶች ከ20 ዓመት በታች "የድሪም ማይል" የዓለም ክብረ-ወሰን ሰበረች

12 Mons Ago
አትሌት ብርቄ ኃየሎም በሴቶች ከ20 ዓመት በታች "የድሪም ማይል" የዓለም ክብረ-ወሰን ሰበረች

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ብርቄ ኃየሎም ትናንት ሌሊት በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደው ዲያመንድ ሊግ ከ20 ዓመት በታች "የድሪም ማይል" የዓለም ክብረ-ወሰንን በመስበር አሸነፈች።

የ17 ዓመቷ ብርቄ ርቀቱን ያጠናቀቀችበት ሰዓት 4፡17.13 ሲሆን፣ ክብረ-ወሰኑ ሂደቱን ጠብቆ እንደሚጸድቅ ከዓለም አሌትክስ የፌስቡክ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። 

አትሌት ብርቄ ያሻሻለችው ክብረ-ወሰን እ.አ.አ በ1994 በአየርላንዳዊቷ ኦሱሊቫን ሶኒያ 4:17:25 ተይዞ የነበረውን - ሲሆን የአሜሪካ እና አውስትራሊያ አትሌቶች በቅደም ተከተል ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በሌላ በኩል በዚሁ በኦስሎ በተካሄደው የ5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል።

አትሌት ዮሚፍ ከኡጋንዳዊው ጃኮብ ኪፕሊሞን ከባድ ፉክክር የገጠመው ሲሆን፣ ርቀቱን 12፡41.73 በሆነ ሰዓት በመግባት አጠናቋል።

ከአትሌት ጃኮብ ኪፕሊሞን ጋር  እኩል በመግባታቸውም ዮሚፍ አሸናፊ መሆኑ የተረጋግጠው በድጋሚ ፎቶ እይታ ነው።

በውድድሩ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ መሆኑን የዓለም አትሌትክስ በትዊተር ገጹ ገልጿል።


ተያያዥ ርዕሶች

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top