በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የተጀመሩ ጥረቶችን ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፦ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

1 Yr Ago
በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የተጀመሩ ጥረቶችን ለማሳካት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል፦ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን

በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የተጀመሩ ጥረቶችን ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።

ኮሚሽኑ በጋምቤላ ክልል ከጋምቤላ ከተማ አስተዳደር፣ ከኢታንግ ልዩ ወረዳ እንዲሁም ከሁሉም ወረዳዎች ለተውጣጡ ተባባሪ አካላት ሥልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ የሥልጠናው ዓላማ፣ ኮሚሽኑ ተልዕኮውን ከግብ ለማድረስ የሚያግዙ ተባባሪ አካላት ስለ ሀገራዊ ምክክሩ እና ስለተሳፊዎች ልየታ በቂ ግንዛቤ አግኝተው የተሰጣቸውን ተግባር እና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል መሆኑን ገልጸዋል።

በሥልጠናው ላይ በተባባሪነት የተለዩ በክልሉ የሚገኙ የሲቪል ማኅበራት ምክር ቤት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት፣ የመምህራን ማኅበር፣ የዕድሮች ማኅበራት ጥምረት፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች የወረዳ አስተዳደር ተወካዮችን ጨምሮ ከሁሉም ወረዳዎች የተውጣጡ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሀገር ሽማግሌዎችም በሂደቱ ወሳኝ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በሥልጠናው በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በሚፍታህ አብዱልቃድር


አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top