ኢትዮጵያና ሕንድ በልዩ ልዩ ወታደራዊ መስኮች በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት በዛሬው ዕለት በባንጋሎር ከተማ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በሕንድ በኩል ደግሞ የመከላከያ ሚኒስትር ራጃንታ ሲንግ ፈርመውታል።
ስምምነቱ በአቅም ግንባታ፣በመከላከያ ጥናትና ምርምር፣ በመከላከያ ኢንዱስትሪዎች፣በሳይበር ደህነንነት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
ይህም የሃገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጠናክረው እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው።
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ህንድ ባዘጋጀችው Aero India 2025 በመሳተፍ ላይ መሆናቸው ይታወቃል።