በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተከናውነዋል፡- አቶ አሻዲሊ ሀሰን

8 Mons Ago 590
በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ተግባራት ተከናውነዋል፡- አቶ አሻዲሊ ሀሰን
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና መልካም አስተዳደር የልማት ዘርፎች ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት ማከናወን መቻሉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርአሻዲሊ ሀሰን ገለፁ።
 
ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የቆየው የክልሉ መንግስት የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወራት የልማት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ተጠናቋል።
 
በመድረኩ አቶ አሻዲሊ ሀሰን እንደገለፁት፤ ክልሉ ተቋማዊ የማስፈፀም አቅምን በመገንባት የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሻሻል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል።
 
በሰላምና ፀጥታ ዘርፍ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ፣ በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እና በገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸው ተገልጿል።
 
የክልሉ መንግስት የሠላም ተመላሾችን ወደ ልማት ስራ እንዲሰማሩማድረጉ እና ሌሎች አበረታች ስራዎች መስራቱንም ጠቅሰዋል።
 
በአንፃሩ በቱሪዝም፣ በመሰረተ ልማት፣ በማዕድን ልማት ላይ የሚታዩ ውስንነቶችን ማሻሻል እንደሚገባ መጠቆሙን የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
 
በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻ ዲሊ ሀሰን፣የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈተረ ቤት ኃላፊ አቶ ኢሳቅ አብዱልቃድርን ጨምሮ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ግብረመልስ
Top